### በማሽንዎ ላይ ጊት(git) ከሌለዎት ፤ [ይጫኑት](https://docs.github.com/en/get-started/quickstart/set-up-git) ።
## ይህንን ማከማቻ **fork** ያድርጉ
በዚህ ገጽ ላይኛው ክፍል ላይ ያለውን የfork button ጠቅ በማድረግ ይህንን ማከማቻ fork ያድርጉት።
ይህ በእርስዎ account ውስጥ የዚህን repository ቅጂ ይፈጥራል።
## የማከማቻውን ተመሳሳይ ይፍጠሩ (Clone)
አሁን fork የተደረገውን ማከማቻ (repository) ቅጂ በማሽንዎ(በኮምፒውተርዎ) ይፍጥሩ። ወደ GitHub (account)መለያዎ ይሂዱ፤ fork የተደረገውን ማከማቻ ይክፈቱ፤ ኮድ የሚለውን button ጠቅ ያድርጉ እና ከዚያ *ወደ clipboard ቅዳ* የሚለውን ጠቅ ያድርጉ::
ተርሚናል ይክፈቱ እና የሚከተለውን የgit ትዕዛዝ run ያድርጉ:
```bash
git clone "የቀዱትን url"
```
"አሁን የገለበጡት url" (ያለ ጥቅስ ምልክቶቹ) የማከማቻው (የዚህ ፕሮጀክት fork) url ነው። urlን ለማግኘት የቀደመውን ደረጃዎች ይመልከቱ።
ለምሳሌ:-
```bash
git clone git@github.com:ይህ-እርስዎ-ኖት/first-contributions.git
```
'ይህ-እርስዎ-ኖት' የእርሶ GitHub ተጠቃሚ username ነው። አሁን በ GitHub ላይ ያለውን የመጀመሪያ አስተዋፅዖ(first-contributions) ማከማቻ ይዘቶችን ወደ ኮምፒውተርዎ እየገለበጡ ነው።
## ቅርንጫፍ ይፍጠሩ
በኮምፒተርዎ ላይ ወዳለው የማከማቻ ማህደር ይግቡ (እዚያው ከሌሉ ማለት ነው!)፡
```bash
cd first-contributions
```
አሁን የ‹git switch› ትዕዛዝን በመጠቀም ቅርንጫፍ ይፍጠሩ፡
```bash
git switch -c የእርስዎ-አዲሱ-ቅርንጫፍ-ስም
```
ለምሳሌ:-
```bash
git switch -c ይሁን-አለማየሁ
```
## አስፈላጊ ለውጦችን ያድርጉ እና ለውጦችን ይፈጥሙ (commit)
አሁን የ‹[Contributors.md](http://contributors.md/)› ፋይልን በጽሑፍ አርታኢ ውስጥ ይክፈቱ እና ስምዎትን ይጨምሩበት። በፋይሉ መጀመሪያ ወይም መጨረሻ ላይ አይጨምሩት። በመካከል የትኛውም ቦታ ላይ ያስቀምጡት። አሁን, ፋይሉን save ያድርጉ።
ወደ የፕሮጀክት ማህደሩ ሄደው ይህን ትዕዛዝ (`git status`) ከፈጸሙ፣ ለውጦች እንዳሉ ያያሉ።
የ‹git add› ትዕዛዙን በመጠቀም እነዚያን ለውጦች ወደ ፈጠሩት ቅርንጫፍ ያክሉ።
```bash
git add Contributors.md
```
አሁን የ‹git commit› ትዕዛዙን በመጠቀም እነዚህን ለውጦች ያድርጉ፡:
```bash
git commit -m "የአስተዋጽዖ አበርካቾች ዝርዝር ውስጥ የእርስዎን-ስም ያክሉ"
```
'የእርስዎን-ስም' የሚለውን በስምዎ ይተኩ፡፡
## ለውጦችን ወደ GitHub ይግፉ
‹git push› የሚለውን ትዕዛዝ በመጠቀም ለውጦችዎን ይግፉ፡፡
```bash
git push -u origin የእርስዎ-ቅርንጫፍ-ስም
```
ቀደም ብለዉ በፈጠሩት የቅርንጫፍ ስም 'የእርስዎን-ቅርንጫፍ-ስም'ን ይትኩ።
remote: Support for password authentication was removed on August 13, 2021. Please use a personal access token instead. remote: Please see https://github.blog/2020-12-15-token-authentication-requirements-for-git-operations/ for more information. fatal: Authentication failed for 'https://github.com/Go to [GitHub's tutorial](https://docs.github.com/en/authentication/connecting-to-github-with-ssh/adding-a-new-ssh-key-to-your-github-account) on generating and configuring an SSH key to your account./first-contributions.git/'
አሁን pull request ያስገቡ።
በቅርቡ ሁሉንም ለውጦችዎን ወደዚህ ፕሮጀክት ዋና ቅርንጫፍ አዋህዳቸዋለሁ። ለውጦቹ ከተዋሃዱ በኋላ የማሳወቂያ 'ኢይሜል' ይደርስዎታል።
## ከዚህስ ወዴት ልሂድ?
እንኳን ደስ ያሎዎት! ልክ እንደ አስተዋጽዖ አበርካች የሚያጋጥሙትን መደበኛ _fork -> clone -> edit -> pull request_ የስራ ፍሰትን አጠናቀዋል!
አስተዋጾዎን ያጣጣጥሙ እና ወደ [ድህረ-ግፅ](https://firstcontributions.github.io/#social-share) በመሄድ ለጓደኞችዎ እና ተከታዮችዎ ያካፍሉ።
ተጨማሪ ልምምድ ከፈለጉ በዚህ ሊንክ [code contributions](https://github.com/roshanjossey/code-contributions) ይግቡ.
አሁን ለሌሎች ፕሮጀክቶች በማበርከት እንጀምር። እርስዎ ሊጀምሩባቸው የሚችሉ ቀላል ጉዳዮች ያላቸውን የፕሮጀክቶች ዝርዝር አዘጋጅተናል። [በዚህ ሊንክ በመግባት በድር መተግበሪያ ውስጥ ያሉትን የፕሮጀክቶች ዝርዝር ይመልከቱ።](https://firstcontributions.github.io/#project-list)
## [ተጨማሪ ቁሳቁስ](docs/additional-material/git_workflow_scenarios/additional-material.md)
## የሌሎች መሳሪያዎች አጠቃቀም አጋዥ ስልጠናዎች
|